በታደሠ በላይ (መጋቢት 26 ፥ 2016 ዓ.ም ፣ ነይረ-አቑ)
የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በአብርገሌ ወረዳ ነይረ-አቑ ከተማ ለሚገኙው የህዝብ ቤተ-መፃህፍት አገልግሎት የሚሰጡ 617 የተለያዩ አጋዥ መፅሃፍትን ድጋፍ አደርጓል። በድጋፉ ወቅት የተገኙት የዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) ዋና ዳይሪክተር ረ/ፕሮፌሰር ሀይሌ ወልዴ እንደሚታወሰው በአብርገሌ ወረዳ በጦርነት የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለማቋቋም ከተለያዮ በጓ አድራጊዎች በድጋፍ የተገኙትን 942 አንደኛ የሁለተኛ እና ደረጃ ትምህርት ቤቶች ማጣቀሻ እና አጋዥ መፅሀፍት ለአብርገሌ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ድጋፍ ያደረግን ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ በአብርገሌ ወረዳ ነይረ-አቑ ከተማ ለሚገኝው የህዝብ ቤተ-መፃህፍት 617 የተለያዩ አጋዥ መፅሃፍት ድጋፍ አድርገናል በማለት ገልጸዋል። ድጋፉን የተረከቡት የአብርገሌ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ ቀለመወርቅ አስማረ እንዳሉት በጦርነቱ ምክኒያት ከ500-700 መፅሀፍት የወደሙብን ሲሆን ይህንን መሰረት በማድረግ “አንድ ሰው ፥ አንድ መፅሀፍ ” በሚል መሪ ቃል በወረዳችንን ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ላይ በማዋል የድጋፍ ጥሪ አድርገናል። በጥሪያችን መሰረት ዋግ ልማት ማህበር (ዋልማ) በዛሬው ዕለት 617 የተለያዩ መፃህፍትን ድጋፍ አድርጎልናል። ልማት ማህበሩ ከዚህ በፊትም በወረዳችን በትምህርት ልማት ዘርፋ ፤ በጤና ልማት ዘርፍ በርካታ ድጋፎችን አድርጓል። በተለያዩ ትምህርት ቤቶች በርከት ያሉ የክላስ የማስፋፊያ ግንባታ ሰርቶልናል።ከዚህ በተጨማሪ “ከዳስ ጥላ ስር ፥ ወደ ክላስ” ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ በተደረገው ግንባር ቀደም ተሳታፊ የነበረ ሲሆን ፤ በየአመቱም የመማሪያ ቁሳቁሶችን በማሟላት አጋዥ ነበር። አሁንም እነዚህ የተለያዩ መጽሃፍትን ለቤተ-መፃህፍቱ በመለገስ አጋርነቱን ያስመሰከረ በመሆኑ እያመሰገንን በቀጣይም ድጋፋችሁ እንዳይለየን በማለት አሳስበዋል። አክለውም የልማት ማህበሩን አረዓያ ተከትላችሁ ሌሎች ግለሰቦች እና ድርጅቶች ድጋፍ እንድታደርጉልን ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
ህብረት ለዋግ ልማት!